ኢዜማ ፓርቲ የምርጫ ምልክቱንና ማኒፌስቶውን አስተዋወቀ!

➖➖➖➖➖➖➖➖
የላንፉሮ ምርጫ ክልል የኢዜማ ፓርቲ ለ7ኛዉ ሀገራዊ ምርጫ የማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክት እንዲሁም የዕጩዎች የማስተዋወቂያ መድረክ አካሄዷል ።
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በላንፉሮ ምርጫ ክልል በጦራ ከተማ ባካሄደው የማስተዋወቅ መድረክ ለቀጣዩ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የሚወዳደርበትን የምርጫ ማኒፌስቶ ለአባላቶችና ደጋፊዎች አስተዋወቀ።
በዕለቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የስልጤ ዞን የኢዜማ ፓርቲ ማስተባበሪያ ምክር ቤት ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ንጉሴ ፍቃዱ እንደገለፁት 7ኛው ሀገር አቀፍ ጠቅላላ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊ ፍትሃዊና ተዓማኒነት ያለው ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል።
መንግሥት አብሮ የመስራት ጥሪ ባቀረበዉ መሰረት የኢዜማ አባላት የመንግሥት ስራ አስፈፃሚ ዉስጥ መካተታቸውን የተናገሩት አቶ ፍቃዱ ይህም ጅምር ስራ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አመላክተዋል።
በዚህም በምርጫ ክልሉ ብሎም በሀገራችን የሚገኙ መራጮች አማራጭ ፖሊሲዎቹን መዝነው ድምፃቸውን እንዲሰጡም ሰብሳቢው ጥሪያቸዉን አቅርበዋል።
ፓርቲው በማኒፌስቶው ላይ የዜጎችን ማህበራዊ ፍትህ ለማረጋገጥ፣ የኢኮኖሚ እድገትን ለማምጣት እና በሀገሪቱ አስተማማኝ ሰላም ለመገንባት ያላቸውን አማራጭ ፖሊሲዎችን አቶ ንጉሴ በዝርዝር አቅርበዋል።
ፕሮግራሙ የፓርቲውን ፖሊሲዎች እና እጩዎችን ለአባላቶችና ደጋፊዎች ማስተዋወቅ ችሏል ።
በዚህም ፦
1️⃣ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እጩ አቶ ሱልጣን አልዬ
2️⃣ ሱንከሞ ተማም የክልል እጩ
3️⃣ባህሬ ልግብቾ ለክልል እጩ
4️⃣ሱልጣን ባረቶ ለክልል እጩ
5️⃣ሸይቾ ሽኩሬ ለክልል እጩ
6️⃣ገለቶ ሸ/ጀማል ለክልል እጩ መሆናቸውን ለአባላቶችና ለደጋፊዎች ማስተዋወቅ ችሏል ስል #የላንፋሮ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ዘግቦታል።











Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Get 30% off your first purchase

X
Scroll to Top