ወቅታዊ አለም አቀፋዊ፣ሀገራዊና ካባቢያዊ ነባራዊ ሁኔታዎች ላይ ያጠነጠነ መድረክ ተካሄደ!By lanfuro / April 21, 2026 ሚያዚያ 12/2018ዓ.ም //የሚቶ ኮሚኒኬሽን //በስልጤ ዞን የሚቶ ወረዳ አጠቃላይ አመራር በተገኘበት ወቅታዊ አለም አቀፋዊ፣ሀገራዊና ካባቢያዊ ነባራዊ ሁኔታዎች ላይ ያጠነጠነ መድረክ ተካሄዷል።ለመድረኩ የተዘጋጀ ሰነድ በወረዳው መንግስት ረዳት ተጠሪ በአቶ ፎሌ ሞሳ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።የስልጠና መድረኩን የመሩት የሚቶ ወረዳ ዋና አስተዳደሪ አቶ ከድር መሀመድና የሚቶ ወረዳ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አብዲ ዋበላ በጋራ መርተዉታል።የሚቶ ወረዳ ዋና አስተዳደሪ አቶ ከድር መሀመድ እንደገለጹት በዓለም የሚታዩ ጂኦ-ፖለቲካዊ አለመረጋጋት እና ተለዋዋጭ አለም አቀፋዊ ሁኔታን መመከት የሚችል ጠንካራ ተግባራትን አቅዶ በመስራት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋጋጥ የአመራሩ ቁልፍ ተግባር መሆን አለባት ብለዋል።በሀገራዊ ደህንነት፣ በኢኮኖሚ፣ በዲፕሎማሲ እና በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ የሚኖሩ ተፅዕኖዎች በየደረጃው ያለው አመራር የህዝቡን ሁላቀፍ ደህንነት አስተማማኝነት ልያረጋግጡ የሚችሉ የልማት ስራዎችን ማከናወን ያስፈልጋል ብለዋል።የሚቶ ወረዳ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አብዲ ዋበላ በአርበኝነት ስሜት የሀገራችንን ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ስትራቴጂያዊ የመሻገሪያ አቅጣጫዎችን በቁርጠኝነት እንዲተገብሩ እና በየደረጃው ያለው አመራር ወቅታዊ ነባራዊ ሁኔታዎች በተገቢው ተገንዝቦ ተግባራትን ስኬታማ ለማድረግ ተቀናጅቶ መስራት አለባት ብለዋል።በየጊዜው የሚፈጠሩ አለም አቀፍ ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን መሸከምና መሻገር የሚችል ማህበረሰብና ኢኮኖሚ መገንባት ያስፈልጋል ያሉት አስተዳዳሪው አለም አቀፋዊ ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን መቋቋም የሚችል የውስጥ ኢኮኖሚ ለመገንባት በወረዳው የተጀመሩ የልማት ስራዎችን በተቀናጀና በተደረጀ መንገድ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።በመድረኩም የሚቶ ወረዳ ዋና አስተዳደሪ አቶ ከድር መሀመድ፣የሚቶ ወረዳ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አብዲ ዋበላ፣የወረዳ አስተባባሪዎች እና የወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል።#መረጃው የሚቶ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ነዉ!